የአካል ነጻነት መብት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት እውቅና ከተሰጣቸው የሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይኸውም የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 17 ድንጋጌ በግልጽ ማንም ሰው በህግ ከተደነገገው ስርአት ውጪ ሊያዝ እንዲሁም ክስ ሳይቀርብበት እና ሳይፈረድበት ሊታሰር የማይችል ስለመሆኑ ያስቀምጣል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት በዚሁ ሕገ መንግስት መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል የሆኑ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነነት ሰነዶችም ቢሆን እውቅና ከተሰጧቸው የሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ ስለመሆኑ እሙን ነው፡፡
ዶ/ር ትዝታ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩዋን ለመከታተል በችሎት ታድማለች፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በቤቷ ላይ ያለአግባብ ፍርድ ተሰጥቷል ብላ ስላመነች የተማረ ጠበቃ የይግባኝ አቤቱታ ጽፎላት ጉዳይዋን በራሷ ትከታተላለች፡፡ እንደ እርሷ አስተሳሰብ ጉዳይዋን ከእርሷ ይልቅ የሚረዳው የለም በሚል ከዳኛ ፊት ቀርባ ለማስረዳት ጓጉታለች፡፡ በዛሬው ቀጠሮ ይህ ሐሳቧ እንደሚሳካላት በውጭ የሚያማክራት ጠበቃ ነግሯታል፡፡
Today, the adjudicatory system of arbitration is replacing the court, since it is considered to be more private, economical, rapid, certain, conducive to business relationships and in some jurisdictions finality of their decision. However, arbitration has its own limitations. For example, arbitrators may make mistakes and all advantages of arbitration may be for the “winners” of arbitration. That is why almost all countries in the globe agreed for the necessity of vacating an arbitral awards in case where the award is defective. The problem is that unlike the arbitration laws of many jurisdictions, the Ethiopian arbitration law has never said anything about the situation after vacating of an arbitral award. And, leaving the post-setting aside situation without adequate procedural rules amounts to exposing the parties for further controversy. So, the main purpose of this article is to examine and analyze the Ethiopian Arbitration Laws governing post-setting aside situation of a vacated arbitral awards. And, the article upholds qualitative legal research which is based on the identification, synthesis and analysis of the law governing vacated arbitral awards. The arbitration laws of other jurisdictions are also overviewed for better understanding of the issues and to indicate where the gap on the arbitration law of Ethiopia is. Finally, the writer recommends the Ethiopian government to refine the arbitration law governing vacating arbitral awards particularly to include a provision that dictate the effects of a vacated arbitral awards.
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 41 አንድ ሰው በተጀመረ ክርክር መብቴ ይነካል፤ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብቼ ልከራከር ብሎ ሲጠይቅ እና በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 418 ለፍርድ ማስፈፀሚያ የተያዘ ወይም የተከበረ ንብረት ይለቀቅልኝ በማለት አቤቱታ ሲያቀርብ የዳኝነት ይከፈላል ወይስ አይከፈልም የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
ተከራካሪ ወገኖች እራሳቸው ወይም በተወካያቸው አማካይነት ፍርድ ቤት በሚወስነው በማንኛውም ቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሳሽ አንድ ጊዜ ጉዳዩን ይዞ ከቀረበ በኋላ ተከታትሎ ከዳር ማድረስ መቻል ያለበት ሲሆን ተከሳሽም በእያንዳንዱ ቀጠሮ እየቀረበ የቀረበበትን ክስ በአግባቡ መከላከል መቻል አለበት፡፡ ክስ ያቀረበ ሰው በሁሉም ቀጠሮዎች እንዲገኝ የሚጠበቅበት ቢሆንም በተያዘው ቀጠሮ ባለመገኘቱ ምክንያት ያቀረበውን ክስ መዝጋት ጨምሮ እንደ ቀጠሮው ምክንያት ሌሎች ትእዛዞች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ክሱ ሊዘጋ የሚችለው ሕጉ ለይቶና ዘርዝሮ ባስቀመጣቸው ምክንያቶችና አጋጣሚዎች ብቻ ነው፡፡ የፍርድቤት ክርክር በከሳሽ እና ተከሳሽ ይሁንታ ላይ ተመስርቶ በፈለጉ ቀን የሚቀርቡበት ደስ ካላላቸው ደግሞ የማይቀርቡበት ሂደት አይደለም፡፡
መኳንንት ከሕግ ትምህርት ቤት ተመርቆ ሲወጣ ግር ያለው ነገር የትምህርቱና የአተገባበሩ ልዩነት ነው፡፡ በአብዛኛው በንድፈ ሐሳብ አስተምህሮና ትንተና ላይ የሚተኮረው ትምህርቱ በተግባር ከሚታየው የፍርድ ቤት ነባራዊ ሁኔታ ጋር አልታረቅ ብሎት ተቸግሯል፡፡ ይህን ችግሩን ያባባሰው ደግሞ ከቤተሰቡ አንዱ የወራሽነት የምስክር ወረቀት ከፍርድ ቤት እንዲሰጠው በማሰብ አቤቱታውን እንዲያዘጋጅለት ሲጠይቀው ነው፡፡ አቤቱታውን አዘጋጅቶ ለቤተሰቡ አባል ቢሰጠውም በአንዱ ክልል ከሚገኘው የወረዳ ፍርድ ቤት የገጠመው ነገር ሌላ ነው፡፡ ቤተ ዘመዱ በፍርድ ቤቱ አቤቱታው በትክክል አለመጻፉ ተነግሮት በፍርድ ቤቱ ደጃፍ ከሚገኙት ራፖር ጸሐፊ ተጽፎ እንዲመጣ ተመከረ፡፡ ሰውየውም የተባለውን ፈጽሞ አቤቱታው ተቀባይነት አግኝቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡ የመኳንንትና የራፖር ጸሐፊው አቤቱታ ልዩነት ቀላል ነበር፡፡
አፈፃፀም ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በእራሱ አማካኝነት ወደ ተግባር የሚለውጥበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የማስፈፀሚያ ሥርዓቱ በጥቅሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ ህጉን መሠረታዊ ዓላማ ተከትሎ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲፈፀም በሚያስችል አኳኋን የተዋቀረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተግባር እንደሚታየው ክስ አቅርቦ ለማስፈረድ ከሚወሰደው ውጭ ጊዜና ጉልበት ባልተናነሰ ሁኔታ የተፈረደን ፍርድ ለማስፈፀም የሚጠይቀው ወጭና ጊዜ በልጦ የሚታይበት ጊዜ ይከሰታል፡፡ ምክንያቶቹ በርካታ ናቸው፡፡
“Law is nothing else, but the best reason of wise men applied for ages to the transaction and business of mankind” Abraham Lincoln
መነሻ ክስተት
ነገሩ እንዲህ ነው! የሙያ ባልደረቦቼ ደንበኞቻቸው ተከሳሽ በሆኑባቸው የፍትሐብሔር የፍርድ ሂደት ላይ መከላከያ መልሳቸውን ሲያቀርቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(2) (ለ) መሠረት “ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ” መሆኑን እና (ሠ) መሠረት የቀረበው ክስ “በይርጋ የታገደ” መሆኑን ጠቅሰው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን በዋናው ክርክር ላይ ካላቸው መልስ ጋር አያይዘው አቅረበው ነበር፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤቶች በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ክርክር ለመስማት በተያዘ ቀነ ቀጠሮ ከሳሾች ሳይገኙ በመቅረታቸው ምክንያት ጉዳዩን እየመረመሩ የነበሩት ፍ/ቤቶች ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ እንደሚክዱ ከጠየቁ በኃላ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሠረት ክስ ለመስማት በተያዘ ቀነ-ቀጠሮ ከሳሾች ባለመቅረባቸው እና ተከሳሾች ክደው በመከራከራቸው መዝገቡን ዘግተናል በማለት ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
ግምቱ ተለይቶ የሚታወቅ የፍትሐ ብሔር ክርክር ጉዳይ በመያዝ በፍርድ ቤት ክስ የሚመሰርት ወይም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የሚያቀርብ ማንኛውም ተከራካሪ በፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 215/1 እና ስለ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል በ1945 ዓ/ም በተደነገገው ደንብ መሠረት የዳኝነት ክፍያ ይከፍላል። በዚህ ክሱን በከፈተበት ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ደግሞ የይግባኝ አቤቱታውን ይግባኝ ለመስማት ሥልጣን ወዳለው ፍርድ ቤት ያቀርባል። ይህ የይግባኝ አቤቱታ እንዲሰማለት ደግሞ በሥር ፍርድ ቤት የከፈለውን የዳኝነት ክፍያ 50% መክፈል ይጠበቅበታል። የዚህ አጭር ማስታወሻ ዓላማም የዚህ የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብ የማይሆንበትን ኹኔታ መጠየቅ ነው።
የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት ከሙግት በፊት ያሉ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደቶች አንድን ክርክር ላይ ያላቸዉን ሚና ማጉላት እና ፋይዳቸዉን ማሳየት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ሂደት ቅደመ ሙግት የሚባለዉ ለክርክሩ መሪ ጭብጥ ተይዞ ግራ ቀኙ ማስረጃ ማሰማት ከመጀመራቸዉ በፊት ያለዉ ሂደት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ዋናዉ ሙግት የሚጀምረዉ ጭብጥ ተይዞ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 257 እና ተከታይ ድንጋጌዎቹ ተከራካሪዎች ማስረጃዎቻቸዉ የሚያስረዷቸዉን ጭብጥ እያስመዘገቡ ማስረጃ ማሰማት ሲጀምሩ ነዉ፡፡ ከዋናዉ ሙግት በፊት ባለዉ የቅድመ ሙግት ሂደት በዋናነት ክስና ማስረጃ ማቅረብ፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መልስ እና ማስረጃ መቅረብ፣ ክስ መሰማት እና የክስ መቃወሚያዉ ላይ የመወሰን ተግባሮች ይፈፀማሉ፡፡ ይህ የክርክር ሂደት ክርክሩን ለመምራት ዋና መሰረት የሆነዉ ነዉ፡፡ የክርክሩ አቅጣጫ የሚወሰነዉም በዚህ የክርክር ደረጃ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ነዉ፡፡ ክርክሩን ግልፅ እና አጭር በሆነ ሂደት ለመፈፀም የሚያስችለዉም የቅድመ ሙግት ሂደቱ ጤናማ መሆን ከቻለ ነዉ፡፡