ጸሐፊው ቀደም ሲል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለአምስት ዓመት ያህል በረዳት ዳኝነት የሠሩ ሲሆን አሁን በጠበቃነት እና በሕግ አማካሪነት እየሰሩ ይገኛሉ።

በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ቤት የሰራ ሰው መብት - አንዳንድ ነጥቦች 
ፈቃዱ ዳመነ ለገሰ
Property Law Blog
ሲፈጠር የአንድ ቤተሰብ የነበረው መሬት ቤተሰቡ በቢሊዮን ሲራባ አንድ ኢንች አልጨመረም። በመንኮራኩር ሰማይ ቢታሰስ በሮኬት ጠፈር ቢሰነጠቅ በምድር ላይ እንዳለው ያለ መሬት እስካሁን አልተገኘም። በምድር ያለው መሬትም በተለያዩ ምክንያቶች ጠቀሜታው እየቀነሰ፣ ለምነቱ እየጠፋና እየጠበበ ይገኛል። መሬት በገጠርም ሆነ በከተማ ዋነኛ የመብት ምንጭ እና የሁሉም ምጣኔ ሀብታዊ፣ ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች መሰረት ነው። እያለቀ የሄደውን መሬት እየጨመረ ላለው ሕዝብ በሚዛን ለማከፋፈል በተለያዩ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት ልዩ ልዩ ፍልስፍናዎች ሲፈለሰፉ፣ ርዕይዎተ ዓለም ሲሆኑ፣ ወደፖሊሲ ሲቀየሩና ሕግ እየሆኑ ሲተገበሩ ቆይተዋል። እየተተገበሩም ይገኛሉ። ይሁን እንጂ በዚህ ዘመን ለሁሉም ዜጎች መሬት መስጠት የሚያስችል ምንም ዓይነት ፍልስፍና አልተገኘም። 
Continue reading
የወራሽነት ማረጋገጫ፣ መቃወሚያ እና ልጅነት፡- ክፍተተ ወሕግ ወአሰራር እና መፍትሔዎቻቸው
ፈቃዱ ዳመነ ለገሰ
Succession Law Blog
የርዕሰ መዲናዋን አስተዳደር ለመመስረት በቻርተር ደረጃ የወጣው አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41(1) (ሸ) እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 408/96 አንቀጽ 2 የወራሽነት ማረጋገጫን ጨምሮ ሌሎች ምስክር ወረቀቶች የመስጠት የስረ ነገር ስልጣንን ለአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ከሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት ዓመተ ምህረት ጀምሮ እስካሁን ድረስ እነዚህ ፍ/ቤቶች እገሌ የእገሌ ወራሽ ነው፣ አንቺ የእንትና ሚስት ነበርሽ፣ አንተ ደግሞ የእገሊት አበዋራ ነበርክ …….. ወዘተ እያሉ በሕግ ዓይን ህያው ይሆን ዘንድ በሞት የፈረሰን የዓይነ ስጋ ዝምድና በወረቀት ማረጋገጫ ሲቀጥሉ ኖረዋል።
Continue reading
በኢትዮጵያ የብድር ሕግ "አበደረ" ማለት የብድሩን ገንዘብ ሰጠ ማለት ይሆን?
ፈቃዱ ዳመነ ለገሰ
Contract Laws Blog
ብድር የሰው ልጅ እና ጎደሎው ከተገናኙበት ሩቅ ዘመን ጀምሮ የነበረ ሰዋዊ ድርጊት ነው፡፡ የብድር መሰረቶቹ መቀራረብ ፣ እዝነት እና መተማመን ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን እነዚህ መሰረቶቹ እየተናጉ የብድርን ህልውና ሲፈታተኑት ይስተዋላል፡፡ በርካታ ሰዎችም ብድርን መሰረት ላደረጉ ክርክሮች ሲዳረጉ ይታያሉ፡፡ ከእነዚህ በርካታ ብድር ነክ ክርክሮች አንዱ በውሉ ላይ ተበዳሪ ተብለው የተሰየሙ ሰዎች የብድሩን ገንዘብ አልተቀበልኩም በማለት የሚያነሱት ክርክር ነው፡፡ ተበዳሪው በውሉ ላይ ተበድሬአለሁ ብሎ የፈረመ ቢሆንም ውሉ ፍ/ቤት ሲመጣ ግን ተበድሬአለሁ ብዬ ፈርሜአለሁ ግን የብድሩን ገንዘብ አልተቀበልኩም ማለት ይከራከራል፡፡
Continue reading