አፈፃፀም ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በእራሱ አማካኝነት ወደ ተግባር የሚለውጥበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የማስፈፀሚያ ሥርዓቱ በጥቅሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ ህጉን መሠረታዊ ዓላማ ተከትሎ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲፈፀም በሚያስችል አኳኋን የተዋቀረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተግባር እንደሚታየው ክስ አቅርቦ ለማስፈረድ ከሚወሰደው ውጭ ጊዜና ጉልበት ባልተናነሰ ሁኔታ የተፈረደን ፍርድ ለማስፈፀም የሚጠይቀው ወጭና ጊዜ በልጦ የሚታይበት ጊዜ ይከሰታል፡፡ ምክንያቶቹ በርካታ ናቸው፡፡
የፍርድ ቤቶችን ችግር ለመፍታት፣ ጫናቸዉን ለመቀነስ፣ የሚያቀርቡትን የዳኝነት አገልግሎት ጥራት ለመጨመር ከሚቀርቡት የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል አማራጭ የሙግት መፍቻ ስልቶችን (ለምሳሌ ግልግል ዳኝነት) ማበረታት ነዉ። አማራጭ ስልቶችን ማበረታታት ተገቢ ነዉ፣ ጠቃሚ እስከሆነ ድረስ። ነገር ግን ፍርድ ቤቶች በችግሮች በተተበተቡበት ሁኔታ፣ ምንም እንኳን ሕጉ ለአማራጭ ስልቶች እውቅና እና ድጋፍ ቢሰጥም፣ የፍድ ቤቶችን ችግር በመፍታት ወይም አለመግባባትን በመቀነስና በመፍታት ረገድ ግን የሚፈይደው ነገር ጥቂት ነው፡፡
የግብይት እና የምርት ወጪ የሚባሉ ሁለት መሰረታዊ ወጪዎች አሉ። የምርት ወጪ የምትለው፥ አንድን አገልግሎት ወይም ሸቀጥ ወይም ነገር ለማምረት የምታወጣው ነው። ቋሚ እና ተቀያያሪ ወጪ ሊሆን ይችላል። ቋሚ የሚባለው ወጪ መጠን፥ በምርትህ መጠን አይወሰነም እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ። ስለዚህ አንድም አመረትህ ሺተሚሊዮን ቋሚ ወጪዉ ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ ብዙ ማምረት ከመጠን እንድትጠቀም ያደርግሃል። ነገር ግን ምን ታመርታለህ? ምንድን ነው ፍላጎትህ? ያመረትከውንስ ለማን እና በምን ያህል ትሸጣልህ? ግብይት ከማን ጋር ትፈጽማለህ? በድርድር ሂደት ያኛው ተዋዋይ ወገን የሚነግርህን መረጃ እንዴት ታረጋግጣለህ? ያኛው ሰውየ ያልነገረህ መረጃ ስለመኖሩ እንዴት ታረጋግጣለህ? እንዴት ትደዳደራለህ? ስምምነት ከገባህ በዃላ ያኛው ሰው ግዴታውን ለመወጣቱ ምን ማረጋገጫ አለህ? ግዴታውንስ በተባለው መጠን እና ጥራት ስለመወጣቱ እንዴት ትከታተላለህ? እነዚህ ሁሉ የግብይት ወጪ ይባላሉ።
የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና ትኩረቱን በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 ላይ በማድረግ አዋጁ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት በአንቀፅ 55(1) ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከተሰጠው ሕግ የማውጣት ስልጣን ጋር ያለውን ተቃርኖ እና የሕገ መንግስቱን የበላይነት ያላከበረ ስለመሆኑ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ተጠሪነት ላይ የሚነሱ የሕግ ጉዳዮችን በመዳሰስ መፍትሔውን ማስቀመጥ ነው፡፡
ከዚህ በፊት ባለው ጽሁፍ የሚከተሉትን ሃሳቦች አቅርቤ ነበር። በዋናነት የእነዚህ ሃሳቦች ተግባራዊነት ዉጤት፤ አሁን ተበጣጥሶ የሚገኘውን በገጠር መሬት ላይ የግብርና ውሳኔ መብት በአንጻራዊነት እንዲማከል ማድረጉ ነው። የግብርና ውሳኔ ማለት፥ በአንድ እርሻ ላይ ምን ላምርት? መቼ ላምርት? ምን አይነት እና መጠን ያለው ማዳበሪያ ልጠቀም? ምን አይነት የውሃ ቴኬኖሎጂ ልጠቀም? ምን አይነት ማረሻ፥ ማጨጃ፥ እና መውቂያ ልጠቀም? ምን አይነት የመሬትና አፈር ጥበቃና አስተዳደር አሰራሮችን ልከተል? እና የመሳሰሉት ናቸው። ከግብርና ውሳኔዎች ጋር የሚገናኙ የገበያ ውሳኔዎች ይኖራሉ። ለምሳሌ፤ ምን ያህል ምርቴን፥ መቼ፥ ለማን ልሽጥ? ምን ያህል ገንዘብ፥ ከማን፥ በምን ያህል ወለድ ልበደር? እነዚህና የመሳሰሉት ገበያ ነክ ውሳኔዎች ካነሳኋቸው ነጥቦች ጋር በቀጥታ አይገናኙም። እኔ ያነሳሁት የግብርና ውሳኔዎችን ነው።
ግብርና የሃገራችን ወሳኝ የኤኮኖሚ ዘርፍ ነው። ምጣኔ ሃብት ምሁሮች እንደሚሉት፥ በቅጥርና አገራዊ ምርት የግብርናው ድርሻ እንዲቀንስ (በሌሎች ዘርፎች እንዲተካ)፥ ግብርናው በፍጥነት ማደግ አለበት። ለማነስ፤ በፍጥነት ማደግ። የግብርና እድገት ምን ይጠይቃል? የመስኖ መሰረተልማት። የተሻሻለ ግብአት፥ ምርጥ ዘር፥ ማዳበሪያ፥ አረም ማጥፊያ። የምርት ገበያ። መሬት። ጉልበት። እውቀት። የገጠር መንገድ። የአርብቶ እና አርሶ አደሮች ትምህርት። የገጠር የጤና አገልግሎት። የገጠር የመጠጥ ውሃ አገልግሎት። የገጠር ሃይል አቅርቦት። የገጠር ሰላምና ደህንነት ማስከበር። የግብርና ግብይቶችን እና ድርጅቶችን መጠበቅ።
ስለሪጉላቶሪ መሳሪያዎች መግቢያ
ዛሬ የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሁለት ብሮድካስተሮች ጽፈውታል የተባለ ደብዳቤ በፌስቡክ መለጠፉን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተስተናገዱ ነው። በደብዳቤው ብሮድካስተሮቹ ለምን የቅዳሜውን የድጋፍ ሰልፍ እንዳላስተላለፉ መረጃ በተጠቀሰው ቀን ይዘው በመምጣት ከባለሥልጣኑ ጋር እንዲወያዩ ያሳስባል። ባለሥልጣኑ ይህን ደብዳቤ “ሊመልሰው፣ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል”፣ እና የመሳሰሉት አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ። የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ምንም እንኳን በሚዲያ ተቋማት ዙሪያ የግሌ ጠቅላላ አስተያየትና እምነት ቢኖረኝም የብሮድካስቲንግ አዋጁን አስመልክቶ ያለኝን ግንዛቤና አረዳድ እንደሚከተለው አካፍላለሁ።
የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 እራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ከአዲስ አበባ እና ከድሬዳዋ ከተሞች ላይ የገፈፈ ስለመሆኑ እና የመፍትሔ አቅጣጫዎቹ፡፡ እራስን በራስ የማስተዳደር መብት የፌዴራል ሥርዓትን በሚከተሉ አገሮች የተለመደ አሰራር ሲሆን በዋናነትም ክልሎች ወይም ራስ ገዝ አስተዳድሮች ከፌዴራል መንግስቱ ተፅእኖ ውጪ የራሳቸው ሕግ አውጪ፤ ሕግ ተርጓሚ (የዳኝነት አካል) እንዲሁም የህግ አስፈፃሚ አካላት ኖሯቸው በcheck and balance መርህ ክልላቸውን ወይም አካባቢያቸውን የሚያስተዳድሩበት ቁልፍ ቃል-ኪዳናቸው ነው፡፡
The problem of climate change has attracted international attention mainly because of its cross-border effects and the impossibility of solving the problem by a few nations. We know that the global climate is currently changing. Climate change is a long-term shift in the weather statistics (including its averages). For example, it could show up as a change in climate normal’s (expected average values for temperature and precipitation) for a given place and time of year, from one decade to the next. The International Panel on Climate Change (IPCC) has set a target to reduce global greenhouse gas emissions so that the global mean average temperature does not increase by more than 2°C above pre-industrial levels. Vulnerable areas such as parts of Africa, Asia, and the Pacific and Caribbean small island states are already facing the impacts of climate change, and so adaptation and mitigation measures are important.
በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል ለውጥ ካስመዘገቡ አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ የጤና አገልግሎትን በቀበሌ ደረጃ ለማስፋፋት፣ በተለይም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የተቸረውን የጤና ኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተግባራዊ በማድረግ፣ የዓለም መንግሥታት ድርጅትን የጤና የሚሊኒየም ግቦችን ለማሳካት ችላለች፡፡ እንደ አብዛኛው ታዳጊ አገሮች ሁሉ ባለፉት ዓመታት የመንግሥት የጤና ፕሮግራሞችና የአጋር ድርጅት ትኩረቶች ውስጥ ወባ፣ ኤችአይቪ/ኤድስና ሳንባ ነቀርሳ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች የመከላከልና ቁጥጥር ሥራ፣ እንዲሁም የሕፃናትና እናቶች ጤናን ማሻሻል በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የአገሪቱ የበሽታዎች ሥርጭት ሁኔታ በለውጥ ሒደት ላይ ያለ ሲሆን፣ በተለይም በከተማዎችና በዙሪያቸው ባሉ ሥፍራዎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙት የልብ፣ የመተንፈሻ አካላት፣ ስኳርና ካንሰርን የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይጠቀሳሉ፡፡