Font size: +
2 minutes reading time (335 words)

ፍርድ ቤት ቅጣት ማቅለያን ወይም ማክበጃን በሌላ ማቅለያ ወይም ማክበጃ ቀይሮ ማቅለል ወይም ማክበድ ይችላል?

የቅርብ ጓደኛው ጋር ተጠግቶ ይኖር የነበረ ግለሰብ፣ ጓደኛው በሌለበት አሳቻ ሰዓት 10000 ብር የሚገመት ቶሺባ ላፕቶፕ ወስዶ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665(1)በመተላለፍ በስረቆት ወንጀል ተከሶ፣ ክሱን በዝርዝር በማመኑ ጥፋተኛ ይባላል::

የቅጣት ማክበጃ አስተያየት የተጠየቀው ዐቃቤ ሕግ የወንጀሉን ደረጃና እርከን ካስቀመጠ በኋላ “ተከሳሹ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው አስጠግቶ በሚያኖረው የቅርብ ጓደኛው ላይ በመሆኑ በከሐዲነት የፈጸመው ነው፡፡ ስለሆነም በወንጀል ሕግ አንቀጽ 84(1)() መሠረት ከብዶአንድ ርከን ከፍ ብሎ  ይወሰንል” ብሎ ይጠይቃል::

ፍርድ ቤቱ የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ከሰማ በኋላ በሰጠው ዝርዝር ቅጣት ተታ ዐቃቤ ሕጉ አቅርቦ የነበረውን የቅጣት ማክበጃ በተመለከተ “ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው በከዲነት ሳይሆን የተጣለበትን እምነት ወይም ኃላፊነት ያላግባብ በመገልገል በመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀ 84(1)ሀ ሳይሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 84(1)(ለ) መረት የቅጣት ማክበጃውን ቀይረን አክበደናል” ብሎ በመጨረሻተከሳሹ ላይ ሁለት ዓመት ቀላል እስራት ወስኖ መዝገቡን ይዘጋል::

በዚህ ባነሳሁት እውነተኛ የፍርድ ቤት ውሎ ፍርድ ቤቱ ቅጣት ማክበጃውን መቀየሩ አግባብ ነውወይስ አይደለም? የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ፡፡ አግባብ ከሆነስ በምን የግ መረት?

ርግጥ ነው የሀገራችን የሙግት ሥርዓት ‘inquisitorial’ ባሕርይው ያመዝናል፡፡ አንደኛው ተከራካሪ አሸናፊ ሌላኛው ተሸናፊ የሚሆንበት ሳይሆን እውነትን አውጥቶ ፍትሕን የማስፈን ዓለማ ያነገበ ነው፡፡ ዳኛው ተከራካሪዎቹ የሚያቀርቡትን ክርክር መስማት ብቻ ሳይሆን በክርክሩ ሂደት ንቁ ተሳታፊ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ተሳትፎ በግልጽ በሕግ መፈቀድ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ ፍርድ ቤቱ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ በማናቸውም ጊዜ ለምስክር ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 136(4) መሠረት ስለተፈቀደ ነው፡፡ በተጨማሪም ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲሰማ የቀረበው ማስረጃ የሚያስረዳው ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ ሳይሆን ሌላ በፍርድ ቤቱ ስልጣን ሥር ያለና ከቀረበው ክስ አነስተኛ የሚያስቀጣ ሌላ ወንጀል ከሆነ አንቀጹን ቀይሮ ተከላከል ሊለውና ካልተከላከለም ጥፋተኛ ሊለውና ሊቀጣው የሚችለው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 113(2) መሠረት ስለተፈቀደ ነው፡፡ የሙግት ሥርዓቱ ዳኞችን ንቁ ተሳታፊ ቢያደርግም ቅሉ የፍትሕ ሥርዓቱ ‘civil law legal system’ በመሆኑ ግልጽ ሕግ ሲኖር ብቻ ነው የዳኞች ንቁ ተሳትፎ የሚረጋገጠው፡፡ ፍርድ ቤት ወይም ዳኛ ሕግ የማውጣት ሥልጣን የለውም!

ስለዚህም ከላይ ባየነው ጉዳይ ዳኛው ቅጣት ማክበጃውን ቀይሮ ያከበደው በየትኛው የሕግ መሠረት ነው? ርሶስ ይህንን ጉዳይ እንዴት ያዩታል?

×
Stay Informed

When you subscribe to the blog, we will send you an e-mail when there are new updates on the site so you wouldn't miss them.

በኢትዮጵያ ሰው በፍርድ ቤት እና ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ስለሚያዝባቸው ሁኔታዎች
የጋብቻ እና ፍቺ ሕጋዊ ውጤቶች ከተሸሻለው የቤተሰብ ሕግ አንፃር

Related Posts

 

Comments

No comments made yet. Be the first to submit a comment
Already Registered? Login Here
Abebe
Sunday, 24 November 2024