1. ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክስ ስለመስማት (Trial in absentia) ፅንሰ ሃሳብ
ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክስ መስማት (Trial in absentia) ማለት ተከሳሹ በወንጀል ክሱ በፍርድ ቤት ጉዳዩ በመታየት ላይ የሚገኝ ቢሆንም ተከሳሹ ግን በአካል በፍርድ ቤት ሳይገኝ ጉዳዩ በሌለበት በመታየት ላይ የሚገኝ ማለት ነው፡፡ ይህ አይነቱ የህግ ስረዓት በተለያዩ ሃገሮች የሚተገበር ሲሆን በእኛም ሃገር በወንጀል ሥነሥርዓት ህጉ እና በመገናኛ ብዙሃን የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 ላይ በልዩ ሁኔታ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክስ መስማት ተገቢነቱ መታየት ያለበት ከወንጀል ህጉ አላማ፤ ከፍትህ እና ከሰብዓዊ መብት አንፃር ነው፡፡