መግቢያ
አለም ዐቀፍ፣ የግልግል የዕርቅና የሽምግልና ተግባራት መሠረታዊ አላማ፣ ከተለያዩ ሀገራት ዜጐች ወይም ኩባንያዎች ጋር የንግድ ግንኙነት በመሠረቱ ወገኖች መካከል የሚያጋጥም የንግድ አለመግባባትን ከመደበኛው የፍርድ ሂደት ወይም ሥነ-ሥርዓት ውጪ በገላጋዮች፣ በአስታራቂዎች ወይም በሽምጋዮች እንደተዋዋይ ወገኖች ፍላጐት ለመፍታት ጥረት የሚደረግበት አለም ዓቀፋዊ ይዘት ያለውን አሠራር ለማስፈን ነው፡፡