የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ስራ አስፈፃሚ የነበሩት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የ8 ዓመት እሥር የተበየነባቸው ሲሆን፤ ይግባኝ ጠይቀው እስሩ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደርጎላቸዋል፡፡
The issue of trafficking in persons from and within Ethiopia has become a critical issue of concern for the country. The level of concern is clearly reflected in the increased media coverage of the situation of victims of trafficking as well as the measures taken by the government to address the problem through legislative, policy and programmatic mechanisms. While the current attention to the issue is to be commended, there also appears to be some level of confusion as to what trafficking in persons is. The current brief article is an attempt to help clarify the problem.
The attorney-client professional relationship is protected by law in every legal system. The protection conferred to professional privilege serves different purposes. From the human rights protection point of view, confidentiality of information obtained during legal advice or legal proceedings promotes the right to a fair trial, the right to privacy, and the right not to incriminate oneself. It protects citizens from arbitrary encroachment of their rights by investigatory authorities.
Distinct from conventional crimes, “organized crime” involves committing a series of crimes by criminal groups. The offenses range from traditional piracy and the slave trade to present-day cybercrime and nuclear smuggling. The Italian Mafia, the Chinese Triads, the Colombian drug cartels, the Japan Yakuza and the Nigerian Criminal groups are examples of organized criminal groups.
የወንጀል ክስን በማስረጃ አስደግፎ በማረጋገጥ እና ተከሳሽን ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ ጥፋተኛ ማስደረግ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ትልቅ ጥረትና ድካም የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ አንድ ወንጀል ማህበረሰቡ ላይ ሲፈጸም ወንጀሉን የፈጸመን አካል ነቅሶ በማውጣት ለፍርድ በማቅረብ ማስቀጣት የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ አንድ መንግሥት የሕዝብን ሥልጣን ሲቀበል የማህበረሰቡን ሰላም መጠበቅ ከሕዝቡ የተጣለበት ግደታው ነው፡፡ ይህንን ሰላም ለመጠበቅ ደግሞ ወንጀል እንዳይፈፀም ይከላከላል፡፡ ከተፈፀመ በኋላ ፈፃሚውን ለሕግ ያቀርባል፣ ወንጀል ለመፈፀሙ ሊያሥረዱ የሚችሉ ማስረጃወችን አብሮ ያቀርባል፡፡
የኢፌድሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 449፦
449. ፍርድ ቤትን መድፈር
(1) ማንም ሰው በፍርድ ቤት ምርመራ በሚደረግበት ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ፦
ሀ/ ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናውን ላይ ያለን ዳኛ በማናቸውም መንገድ የሰደበ፣ ያወከ ወይም በእነዚሁ ላይ ያፌዘ ወይም የዛተ እንደሆነ ወይም
ለ/ የፍርድ ቤቱን ሥራ በማናቸውም ሌላ መንገድ ያወክ እንደሆነ
ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት ወይም ከሦስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል። ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሳያደርግ ወድያውኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን ይችላል።
በወንጀል ጉዳይ የፍርድ ውሳኔ የሰጠው ፍርድ ቤት በድጋሜ ጉዳዩን ማየት ማለት ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የግዜ ገደብ ሳይኖረው ጉዳዩን በድጋሜ በተለያዩ ምክንያቶች ማየትና በድጋሜ ውሳኔ መስጠት ማለት ነው፡፡ በተለይም በዚህ ዘመን የሐሰት ሰነዶች የመቅረባቸው ጉዳይ እራስ ምታት በሆነበት፣ ሐሰተኛ ምስክርነትን መሠረት በማድረግ በተቃራኒ ተከራካሪ ወገንም ሆነ በፍርድ ቤቱ ሊደረስበት ባለመቻሉ የተሳሳተና የተዛባ የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ዘመን የእነዚህን ሐሰተኛ ማስረጃዎች ግዜ ሳይገድበው የሚያገኝ የወንጀል ጉዳይ ተከራካሪ ወደዛው ፍርድ ቤት በመሄድ የተገኘውን አዲስ ማስረጃ መሠረት በማድረግ ክርክር በድጋሜ አድርጎ ውሳኔው እንዲሰተካከል ለማድረግ የሚያስችል የሕግ አካሔድ መኖሩን አስፈላጊነት ሁሉም የሚስማማበት ነው፡፡ አንዳዴም እንደሚሰማው በህይወት ያለን ግለሰብ ገድለኃል ተብሎ ጥፋተኛ የተባለን ግለሰብ ሞተ የተባለው ግለሰብ በህይወት መኖሩ ቢታወቅ እንኳን ጥፋተኛ የተባለውን ግለሰብ ነፃ የሚያወጣ የሕግ አካሔድ ሊኖር የሚገባ ስለመሆኑም የሚያስማማ ነው፡፡ በቅርብ ግዜ በተላለፈ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ከሚያጋጥማቸው ጉዳዮች በመነሳት የሐሰት ሰነዶች እና የሐሰት ምስክርነት ጉዳይ ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከተ መምጣቱን ሲናገሩ መስማቴ ትዝ ይለኛል፡፡ ይህን መሰል የፍትሕ ጠር የሆነ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ባይቻል እንኳን ይህ ሁኔታ በታወቀ ግዜ ግን ጉዳዩን ውሳኔውን የሰጠው ፍርድ ቤት በድጋሜ እንዲያይ የሚያስችልና ሐሰተኛውን ማስረጃ እና የተሳሳተውን ውሳኔ ለማስተካከል የሕግ መሠረት ሊኖረን ይገባል፡፡
A criminal law may be changed owing to various reasons. Obsoleteness, loopholes and insufficiency of penalties on the part of the existing criminal law are some of the justifications which may warrant its amendment or replacement. Even though changing a criminal law following changes in circumstances is vital and advisable, the advent of a new criminal law may create the difficulty of determining the temporal scope of application of the former and the new laws. An interesting solution for such problem is the principle of nonretroactivity of criminal law, which states that a criminal law is applicable only to offences committed subsequent to its enactment. Nevertheless, this principle has some exceptions, which allow the retrospective application of a criminal law.
ዋስትና በሕገ መንግሥትም ሆነ የሕገ መንግሥቱ የበታች በሆኑ በርካታ ሕጎች የታፈረና የተከበረ መሠረታዊው ከሆነው የሰው ልጅ የመዘዋወር ነፃነትና ንፁሕ ሆኖ የመገመት መብት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ የሰው ልጅ እንደፈለገ ለመዘዋወር ሁለት እግሮች የተሰጡት፤ በአንድ ቦታ ተወስኖ እንዳይቀመጥ ሰዋዊ ተፈጥሮ ነፃ አድርጎ የፈጠረው ይህን ተፈጥሮውንም አብዝቶ የሚወድ ነፃ ፍጡር ነው፡፡ ይህ ፍጡር አሳማኝ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ አንዳች ወንጀል መፈፀሙ ካልተረጋገጠበት በስተቀር ንፁህ ሆኖ የመቆጠር መብትም አለው፡፡
ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ወንጀል የዚች ዓለም እውነት ነው፡፡ ቃኤል አቤል መግደሉ ከተሰማበት ይህን ጽሑፍ እርሶ እያነበቡ እስካሉት ቅፅበት ድረስ ወንጀል በሰው ልጆች ላይ በሰው ልጅ በራሱ ይፈፀማል፡፡ ይህ ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር መሳ የሆነ ታሪክ ያለው ወንጀል ወደፊትም ማቆሚያ የሚኖረው አይመስልም፡፡ የሰው ልጅ ማድረግ የቻለው ወንጀል የሚቀንስበትን አማራጭ መዘየድ እንጂ ወንጀል አልባ ዓለም መፍጠር አይደለም፡፡ ምናልባትም ወንጀል የመቀነስ ሙከራውም ተሳክቶ እንደሆነ እንጃ፡፡