ዛሬ በጠዋቱ ዜናው በሙሉ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ሲጓዝ የነበረን 202 ሰዎችን ያሳፈረ የኢትዮጵያ አውሮፕላን 'መጠለፍ' ጉዳይ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ‹ጠላፊው ካርቱም ላይ የተሳፈረ ሰው ይመስላል› ቢሉም በመጨረሻ አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ከነጭራሹ እንዳላረፈና ጠላፊውም ረዳት ፓይለቱ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ረዳት ፓይለቱ ለምን ይሄን ተግባር እንደፈፀመ ሲጠየቅም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ስጋት ላይ እንደጣለው በመግለፅ፤ ሲዊዘርላንድ ጥገኝነት እንድትሰጠው ጠይቋል፡፡
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ስራ አስፈፃሚ የነበሩት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የ8 ዓመት እሥር የተበየነባቸው ሲሆን፤ ይግባኝ ጠይቀው እስሩ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደርጎላቸዋል፡፡
የሰው ልጅ ሐሳቡን ለሌላው መግለጽ መጀመሩ ሰዎች የጋራ ባሕርያትን ይዘው ወደ አዲስ ስልጣኔ፤ ወደ አዲስ ሕይወት እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ትስስር ድንበር የለሽ መሆን ጉዳት አለው በማለት፤ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶች መረጃን የመለዋወጡ ሂደት ገደብ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ገደብ እንዲደረግ የሚያስገድዱት ዋነኛ ምክንያቶች ሦስቱን ዋነኛ ተቋማት መጠበቅ በሚል ሐሳብ ስር ይጠቃለል፡፡ እነዚህም ተቋማት ቤተሰብ፣ ቤተ እምነት እና ቤተ መንግሥት ናቸው፡፡ ቤተሰብን መጠበቅ ስንል ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት በመሆኑ ቤተሰብን እና ስርዓቱን የሚጎዱ ነገሮች (Obscene) በአደባባይ እንዳይኖሩ ማድረግ ማለታችን ነው፡፡ ቤተ እምነትን የሚያጎድፉ ነገሮችም (Blasphemous) እንዲሁ:: እንዲሁም በሦስተኝነት በሕግ የተዘረጋውን ስርዓት ለመጠበቅ ሲባል ሲሆን ይሄም የግደባ ሂደት ሳንሱር (Censorship) ይባላል፡፡