(ለጉቦኞች አይላላኩ፤ ከተላኩ ዘብጥያ ይላካሉ!)
ይህ አጭር ጽሑፍ በማወቅም ባለማወቅም የወንጀል አድራጊዎች ተልእኮ የሚያስፈጽሙ ሰዎች እንዲጠነቀቁ ለማስቻል በግርድፉ የቀረበ ነው፤ ጥልቀት ያለው ትንተና እንዳይጠብቁ። ጽሑፉ ሰዎች የቆሸሸ ገንዘብ የሚያቀባብሉበት እጃቸው፣ እንዲሁም የጉቦኞች የገንዘብ መላላኪያ የሚያደርጉት የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው አደገኛ መዘዝ ይዞባቸው እንዳይመጣ ሊጠነቀቁ ይገባል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ፣ ምናልባትም ለማስጠንቀቅ የቀረበ የሕጉ አጭር መግለጫ ነው። ለሕግ ሙያተኞች ፈጽሞ ጥቅም የለውም ማለት ባይቻልም ዓይነተኛ ጥቅሙ ግን ከሙያው ዓለም ውጪ ላለው ለተራው ማኅበረሰብ ነው። ጽሑፉ ስለማቀባበል የሙስና ወንጀል ውስን የግንዛቤ ማስጨበጫ ነጥቦችን በመያዝ ተዘጋጅቷል። ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንምና ይነበብ።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ፀጋ የተከበበች ውብ ሀገር ብትሆንም በድህነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቃ የምትኖር፤ ባደጉ ሀገራት ተረፈ ምርትና የአየር ብክለት ገፈት ቀማሽነት፤ በሚጠጣ ንጹህ ውኃ እጥረት ተጠቂነት የምትነሳ ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ በመአድን፣ በለም መሬት፣ በእንስሳት፣ በውኃ ኃብት እንዲሁም በሌሎች አላቂና አላቂ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለፀጋ መሆኗን የሚካድ ባይሆንም በተፈጥሮ የታደለችውን ኃብት ጥቅም ላይ ከማዋል ረገድ ግን እምብዛም አይደለችም፡፡ ሜዳዋንና ተራሯን የሚሸፍን የተፈጥሮ ዝናብ እየተቀበለች ይህ ዝናብ አፈሯንና ወርቋን ጠራርጎ በመውሰድ ለጎረቤት ሀገራት ነፃ ስጦታና ችሮታ እንዲሆን ከመፍቀድ ውጪ የልማት መንገዱን አልተገለጠላትም፡፡ ወንዞች በደራሽ ውኃ ተጥለቅልቀው የገበሬ ማሳ የጎርፍ ሲሳይ ሲያደርጉ ማየት ክረምት በመጣ ቁጥር የምንገነዘበው መራራ እውነት ነው፡፡ አባይን የሚያክል ግዙፍ የውሀ ኃብት ከጉሮሮዋ እየፈለቀቁ የራሳቸው ከርሰ ምድር ሲሞሉ ኢትዮጵያ የበይ ተመልካች ሆና መኖሯን ግርምት ይፈጥራል፡፡
ጊዜው እ.ኤ.አ 1954 ነው፡፡ ለአለም ሀገራት የዲሞክራሲ አርአያና መምህር ነኝ ብላ በምትደሰኩር በአሜሪካ ሀገር ነጭና ጥቁር ተማሪ በአንድ ላይ አይማርም ነበር አሉ፤ ምክንያቱም ጥቁር ተማሪ ከነጭ ተማሪ ጋር በአንድ ላይ እንዲማር መፍቀድ ማለት በነጭ ተማሪዎች ሞራልና ክብር መቀለድ ነው ብላ ታምን ነበር፤ አሜሪካ፡፡ በመሆኑም ጥቁሮችና ነጮች ተለያይተው ይማሩ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚሁ አይን ያወጣ አድልዎ የተበሳጨው ብራውን የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ ሀገር የካንሳስ ክልል የትምህርት ጉዳይ ቦርድን በፍርድ ቤት ገተረው፡፡ ሚስተር ብራውን ለጥቁሮች ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኃላ ጥቁሮችን አንገት የሚያቀና ፍርድ አስፈረደ፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቁርና ነጭ ተማሪዎች ተለያይተው እንዲማሩ ማድረግ የሰው ልጆች በተፈጥሮ እኩል ሆኖው የመፈጠር መብትን የሚቃረን በተለይም ደግሞ የጥቁሮች ክብርና ሞራል የሚነካ እኩል የትምህርት እድል የሚነፍግ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ ከተፈጥሮ ሕግና የአሜሪካ ህገ መንግስት ጋር የሚጣረስ ነው ሲል ለሰው ልጆች እኩልነት የሚያረጋግጥ ፍርድ ሰጠ፡፡ ጥቁሮች ከነጮች ጋር ያለአድልዎና ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩል የትምህርት እድል የማግኘትና የመማር መብት አላቸው የሚል መደምደሚያ ላይ ተደረሰ፡፡ በዚሁ ውሳኔ የተበሳጨው "ጆርጅያ ኩሪዬር" የተባለ ጋዜጣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ዳኞችን እንዲህ ሲል ገለፃቸው፡፡
(‘ደረሰኝ የማይሰጥ ከሆነ አይክፈሉ')
ደረሰኝ ምን ማለት ነው?
የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19፣120 እና 131(1)(ለ) እንዲሁም የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 82 ላይ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ጣምራዊ ንባብ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች መሠረት በማድረግ የደረሰኝ ትርጉም እና ምንነት፣ የደረሰኞች ዓይነቶች እና ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ግብር ከፋዮችን እነማን እነደሆኑ እንዲሁም ደረሰኝ መሰጠት ያለበት መች እንደሆነ በወፍ በረር መልኩ ለመዳሰስ እሞክራለሁኝ፡፡