ሰዎች ኑሮአቸውን ስኬታማ ለማድረግ በሚፈጽሙት የእለት ተእለት ተግባራቸው ከሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎች ጋር ዘርፈ ብዙ መስተጋብሮችን የሚፈጽሙ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይሁንና እነኚህን መስተጋብሮች በተለያዩ ምክኒያቶች በራሳቸው ለመፈጸም የማይችሉ በሆነ ጊዜ ሥራዎችን ሌላ ሰው እንዲያከናውንላቸው ፍላጎት ሊያድርባቸው እንደሚችል የሚያሻማ አይደለም፡፡ በዚሁ መሠረት ይህንኑ ሥራቸውን ማን፣ መቼ፣ በምን ሁኔታ እና በድካም ዋጋ ክፍያ ወይም ያለ ክፍያ ሊሠራላቸው እንደሚገባ የመወሰን ነጻነት ሊኖራቸው የተገባ ነው፡፡