ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ወንጀል የዚች ዓለም እውነት ነው፡፡ ቃኤል አቤል መግደሉ ከተሰማበት ይህን ጽሑፍ እርሶ እያነበቡ እስካሉት ቅፅበት ድረስ ወንጀል በሰው ልጆች ላይ በሰው ልጅ በራሱ ይፈፀማል፡፡ ይህ ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር መሳ የሆነ ታሪክ ያለው ወንጀል ወደፊትም ማቆሚያ የሚኖረው አይመስልም፡፡ የሰው ልጅ ማድረግ የቻለው ወንጀል የሚቀንስበትን አማራጭ መዘየድ እንጂ ወንጀል አልባ ዓለም መፍጠር አይደለም፡፡ ምናልባትም ወንጀል የመቀነስ ሙከራውም ተሳክቶ እንደሆነ እንጃ፡፡
አንድ ሰው ወንጀል በመስራት በመጠርጠሩና የተጠረጠረበት ወንጀል በሕጉ ዋስትና የማያስፈቅድ በመሆኑ ወይም በዋስትና ለመውጣት አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች እስኪከናወኑ ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ እስረኛው በሕጉ የተፈቀደለት የሰብአዊ ክብር እንክብካቤና በሕይወት ለመቆየት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ እየተሟሉለት የፍርድ ሂደቱን የመከታተል መብት አለው፡፡ እስረኛው በፍ/ቤት ወንጀለኛ ተብሎ ያልተፈረጀ ይልቁንስ በህገመንግስቱ አንቀፅ 20/3/ መሠረት ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት ያለው በመሆኑ ተገቢው ክብርና እንክብካቤ የሚገባው ነዉ፡፡
እናትነት እውነት አባትነት ግን እምነት ነው የሚለው አባባል ተደጋግሞ የሚሰማው አባትነትን ማረጋገጥ ፈታኝ የሆኑ ማህበራዊ ባይሎጂካዊና ሕጋዊ ውስብስብነት ያለው ፈታኝ ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡ አባት ለልጁ ግዴታዎችን አሉበት፤ አባት ከልጁ የሚጠይቀው መብት አለው፡፡ ልጅ ለአባቱ የሚጠይቀው ግዴታዎች ያሉበትን ያህል ከአባቱም የሚጠይቀው መብት አለው፡፡ እኚህ በመሀላቸው መብትም ግዴታም ያስተሳሰራቸው ሁለት ሰዎች ታዲያ በርግጥም አባትና ልጅ ናቸው? የሚለው ጥያቄ ፈታኝ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከባድ ስለመሆኑ አባትነትንና ልጅነትን ስለማወቅ በሕጉ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ለጥያቄው ምላሽ በሚሰጡበት አካሔድ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ጽሑፍም የሚያጠነጥነው ከጋብቻና እንደባልና ሚስት አብሮ ከመኖር ግንኙነት ውጭ በአንድ አጋጣሚ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ምክንያት የተወለደን ልጅ በተመለከተ ሆኖ በእንደዚህ ዓይነት ግንኙነት የተወለደ ልጅ በርግጥ በሕግ አይን አባት አለው? ካለውስ ሕጉ በዚህ ረገድ ግልጽና ወጥ ነው? የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 107/2/ በርግጥስ ፋይዳው ምንድን ነው? የሚሉ ጉዳዮችን ለውይይት መነሻ እንዲሆን ያህል ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 ላይ አንድ ምስክር በፖሊስ ምርመራ ወቅት የሰጠው ቃል ዓቃቤ ሕግ ወይም ተከሳሹ ባመለከተ ጊዜ የተሰጠውን ምስክርነት ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ይህ መብት የተሰጠው ለዓቃቤ ሕግ እና ለተከሳሽ በእኩል ደረጃ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ በሚባል አኳኋን እየተጠቀመበት ያለው ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ በማስረጃነት የቆጠረው ምስክር በማንኛውም ምክንያት በችሎት ቀርቦ መመስከር ባልቻለ ጊዜ ሁሉ ዓቃቤ ሕግ የሚጠቅሰው ሥነ ሥርዓት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145ን ነው፡፡ በችሎት የቀረቡ ምስክሮች አጠራጣሪ ወይም የቀረበውን ክስ በሚገባ የማያስረዱ ሲሆን ዓቃቤ ሕግ ፊቱን ወደ 145 ያዞራል፡፡ 145 የዓቃቤ ሕግ የማስረጃ ክፍተት ማሟያ እየሆነ መጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቶችም ይህንንኑ ለፖሊስ የተሰጠ የምስክርነት ቃል በአብዛኛው ተቀብለው በማስረጃት ሲጠቀሙበት ይሰተዋላል፡፡
ዋስትና በሕገ መንግሥትም ሆነ የሕገ መንግሥቱ የበታች በሆኑ በርካታ ሕጎች የታፈረና የተከበረ መሠረታዊው ከሆነው የሰው ልጅ የመዘዋወር ነፃነትና ንፁሕ ሆኖ የመገመት መብት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ የሰው ልጅ እንደፈለገ ለመዘዋወር ሁለት እግሮች የተሰጡት፤ በአንድ ቦታ ተወስኖ እንዳይቀመጥ ሰዋዊ ተፈጥሮ ነፃ አድርጎ የፈጠረው ይህን ተፈጥሮውንም አብዝቶ የሚወድ ነፃ ፍጡር ነው፡፡ ይህ ፍጡር አሳማኝ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ አንዳች ወንጀል መፈፀሙ ካልተረጋገጠበት በስተቀር ንፁህ ሆኖ የመቆጠር መብትም አለው፡፡
በከተማችን ሰማይ ላይ የሰፈረ መንፈስ አለ የሆነ ህጻኑን ወጣቱን አዛውንቱን የሚፈታተን መንፈስ፡፡ በራዲዮ ቢራ፣ በቴሌቭዥን ቢራ፣ በቢልቦርዶች ገፅ ላይ ቢራ ሆኗል ከተማው፡፡ ዛሬ ዛሬ ቢሮ ከሚለው ስም ይልቅ ቢራ የሚለውን ስም መስማት የተለማመደ ሆኗል፡፡ እኔም በእለት ተእለት እንቅስቃሴም ውስጥ በሁለት ነገሮች እርግጠኛ ነኝ ከእሁድ በስተቀር ቢሮ እንደምገባና አንድ የቢራ ማስታወቂያ ጆሮየ እንደሚሰማ፡፡ ከወዳጅ ዘመዶቼ ይልቅ አዲሱ ዓመት መልካም እንዲሆንልኝ አብዝተው የተመኙልኝም የቢራ ማስታወቂያዎች ናቸው፡፡ ቢራ ስትጠጣ አዲሱ ዓመት የሰላም የጤና የብልፅግና ይሆንልሀል ዓይነት ፉገራ እየፎገሩኝ፡፡ ይህን ያህል ቢራ የሕይወታችን ገፅታ ሆኗል፡፡ ስለቢራ ላለመስማት ብር ብሎ ከመጥፋት ውጭ አማራጭ የለም በመዝናናታችን መኃል፣ በመንገዶቻችን ዳርቻ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቻች ቢራ አለ፤ ቢራ መኖሩ አይደለም ችግሩ፣ ችግሩ ቢራ አብዝቶ መኖሩና እየተነገረበት ያለው መንገድ ነው፡፡ ቢራ የማኅበራዊ የሥነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይታችን ጋሬጣ ሊሆነ በሀገሪቱ ሰማይ ላይ አንዣቧል፡፡